የሶማሊያ ፕሬዝዳንት አዲስ አበባ ገቡ

መስከረም 18/2015 (ዋልታ) የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ።

ፕሬዝዳንቱ ቦሌ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ የሁለቱ ሀገራት እና ቀጣናዊ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ፕሬዝዳንቱ ከሦስት ወራት በፊት በተደረገ ምርጫ አሸንፈው ወደ ስልጣን መምጣታቸው ይታወሳል፡፡

በመስከረም ቸርነት

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW