የሸዋል ኢድ በዓል ማጠቃለያ መርኃ ግብር እየተካሄደ ይገኛል

ግንቦት 2/2014 (ዋልታ) ከኢድ እስከ ኢድ መርሐ ግብር አካል የሆነውውና ከሚያዚያ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በሀረሪ ክልል ሲከበር የነበረው  የሸዋል ኢድ ማጠቃለያ መርኃ ግብር  እየተከናወነ ነው።

በማጠቃለያ መርኃ ግብሩ ላይ ‘የሸዋል ኢድ በዓል’ የምስራቅ ኢትዮጵያ አጎራባች ክልሎች ይበልጥ አንድነትና ውበታቸውን  ያሳዩበት ነው ተብሏል።

የክልሉ ተወላጅ ዲያስፓራዎችም ሐረር ያላትን እምቅ የቱሪዝም ሀብት ለዓለም ለማሳወቅ መስራት እንደሚገባቸው  በመድረኩ ተነስቷል።

ሱራፌል መንግስቴ (ከሐረር)