የሻደይ በዓል በሰቆጣ ከተማ እየተከበረ ነው

ነሐሴ 16/2014 (ዋልታ) የሻደይ በዓል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በሰቆጣ ከተማ እየተከበረ ነው፡፡

በዓሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንና የአማራ ክልል ርዕስ መስተዳድር ይልቃል ከፋለን (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው እየተከበረ የሚገኘው።

በዓሉ በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ከተማ “ሻደይ ኢትዮጵያ በግንባር፣ ለድል፣ ለአንድነትና ለክብር” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ባለፉት ሁለት ዓመታት በአሸባሪው የሕወሓት ቡድን ወረራና በኮሮና ቫይረስ ስርጭት ምክንያት የሻደይ በዓል በአደባባይ ሳይከበር መታለፉ ይታወሳል።