የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ በአማራ ክልል የትምህርት ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ

የካቲት 15/2013 (ዋልታ) – ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ በአማራ ክልል ለሚገኙ የትምህርት ተቋማት የሚያገለግሉ የትምህርት ቁሳቁሶችን ለአማራ ወጣቶች ማህበር አስረክቧል።

የስፖርት ክለቡ የሬዲዮ ክፍል ኃላፊና የህዝብ ግንኙነት ተወካይ አቶ ካሳሁን ደርቤ ሀገር መረጋጋት ስትጀምር ትውልድ መማር ስለሚቀጥል ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

በዚህም 50 ሺህ ደብተሮች እና ከ30 ሺህ በላይ እስክርቢቶና ሌሎች ለትምህርት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን  ለተቸገሩ ወገኖች እንዲደርስ በማሰብ ማበርከታቸውን የአማራ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል።