የቅድመ ጎርፍ መከላከል ላይ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን አስመልክቶ ውይይት እየተካሄደ ነው

ሰኔ 19/2013 (ዋልታ) – የተፋሰሶች ልማት ባለስልጣን ከክልልና ከሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የክረምቱን መግባት ተከትሎ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ሊከሰቱ የሚችሉ የጎርፍ አደጋዎችን መከላከል እንዲቻል ቀድመዉ የተሰሩና መሰራት ያለባቸዉ ስራዎች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ዉይይት እየተካሄደ ነው።
የተፋሰሶች ልማት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዳነች ያሬድ (ዶ/ር) ከዚህ ቀደም የነበሩ የጎርፉ አደጋዎችን መሰረት በማድረግ ጎርፍ ሊከሰትባቸው ይችላል የተባሉ ቦታዎችን በመለየት ጎዳቱ ሳይደርስ መከላከል የሚያስችል የቅድመ መከላከል ዝግጅት ሥራ መሰራቱን አንሰተዋል።
የዉሃ መሰኖና ኢነርጅ ሚኒስትር ዴኤታ አብርሃ አዱኛ(ዶ/ር) በበኩላቸዉ ከመስከረም ጀምሮ የቅድመ ጎርፉ መከላከል ሰራዉ ሲሰራ መቆየቱን ጠቅሰዉ፣ አሁንም የተቀናጀ ሥራ ለመሰራት አሰፈላጊዉ ዝግጅት ስለመደረጉ ገልፀዋል።
ባለፈው ዓመት በተለያዩ አካባቢዎች ተከሰቶ የነበረዉን የጎርፍ አደጋ ለመከላከል ከሁሉም ከልሎች ጋር የረጅም፣ መካከለኛና የአጭር ጊዜ እቅድ በማዘጋጀት በሰዉ ህይወትና በንብረት ላይ የሚደርሱ አደጋዎችን ለመከላከል እንዲያስችል ከህቡረተሰቡ ጋር በመሆን የቅድመ መከላከል ሥራዎቸ መከናወናቸውን ገልፀዋል።
(በህይወት አክሊሉ)