ሐምሌ 10/2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃግብር አካሄደ፡፡
ተቋሙ በሉሜ ወረዳ ጠዴ ቀበሌ ወረዳ በ14 ሄክታር መሬት ከ3 ዓመት በፊት አንስቶ ችግኝ መትከል መጀመሩ ተገልጿል፡፡
ዘንድሮም ለ3ኛ ጊዜ የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች ከሌሎች አጋር ተቋማት ጋር በመሆን በአካባቢው አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡ በመርኃግብሩ 26 ሺህ ችግኞች መዘጋጀታቸውም ተጠቁሟል፡፡
በችግኝ ተከላ መርኃግብሩ ላይ የሞጆ ደረቅ ወደብ እንዲመሰረት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረጉት የቀድሞ የትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስትር ጁነዲን ሳዶና የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ ሮባ መገርሳ ተገኝተዋል፡፡
(በሳሙኤል ሀጎስ)