መጋቢት 29/2014 (ዋልታ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የቦርድ አባላት ሹመትን አፀደቀ፡፡
ምክር ቤቱ ባለሥልጣኑን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 1238/2ዐ13 መሠረት ነው ያፀደቀው፡፡
በዚህም መሰረት
- አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ ሰብሳቢ
- አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ከቱሪዝም ሚኒስቴር፤ አባል
- አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር ከዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል፤ አባል
- አጋረደች ጀማነህ (ዶ/ር) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፤ አባል
- በድሉ ዋቅጀራ (ዶ/ር) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፤ አባል
- መሣይ ገ/ማሪያም (ዶ/ር) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፤ አባል
- ወዳጀነህ ማዕረነ (ዶ/ር) አማካሪ፤ አባል
- ቀሲስ ታጋይ ታደለ ከሃይማኖት ተቋማት፤ አባል
- ኡስታዝ ያሲን ኑሩ ከሃይማኖት ተቋማት፤ አባል ሆነው በውሳኔ ቁጥር 8/2ዐ14 በ11 ተቃውሞ እና በ17 ድምፀ ታአቅቦ በአብላጫ ድምፅ የፀደቀ ሲሆን በዚህም መሠረት ተሿሚዎቹ ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።