የባሕል ቡድኑ ለሠራዊቱ የማነቃቂያ ዝግጅት እያቀረበ ነው

ነሐሴ 10/2013 (ዋልታ) – የወሎ ላልይበላ የባሕል ቡድን በግንባር ተገኝቶ ለሠራዊቱ የማነቃቂያ ዝግጅት እያቀረበ ነው።

ከወሎ ላልይበላ የኪነት ቡድን በተጨማሪ ካቤናት ኢትዮጵያ እና ውብ ኢትዮጵያ መልቲ ሚዲያዎች ከአዲስ አበባ በጎ ፈቃደኛ ድምፃዊያንንና የውዝዋዜ ባለሙያዎችን አስመጥተዋል።

ድምፃዊያኑና ተወዛዋዦችም ሠራዊቱን እያበረታቱ ሲሆን የኪነ ጥበብ ባለሙያዎቹ ሠራዊቱ የመጨረሻውን ድል እስኪቀናጅ ድረስ ከጎኑ እንደማይለዩም አረጋግጠዋል።

የኪነጥበብ ባለሙያዎቹ ጉዳዩ የሀገር ጉዳይ ነው፣  ሁሉም የኪነጥበብ ባለሙያ ሠራዊቱን  ሊያበረታታ ይገባል ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡