የብልጽግና ፓርቲ ለመከላከያ ሰራዊት የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

ብልጽግና ፓርቲ

ታኅሣሥ 11/2014 (ዋልታ) የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት ለአገር መከላከያ ሰራዊት የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡

ጽህፈት ቤቱ ከዚህ ቀደም የዘማቾችን ሰብል በመሰብሰብ እና ለዘማች ቤተሰቦች ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በዛሬው እለትም የመኝታ ቁሳቁስ፣ የቴምር እና የንጽህና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡

የፓርቲው አመራሮች በኢፌዴሪ መከላከያ ዋር ኮሌጅ በመገኘት ድጋፉን ያስረከቡ ሲሆን በስነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የጥናትና ምርምር ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ተመስገን ቡርቃ (ዶ/ር) ምትክ የሌለውን ህይወቱን ለሀገሩ ለመሰዋት ዝግጁ ለሆነው መከላከያ ሰራዊት የሚደረገው ድጋፍ ቀጣይነት እንዳለው ገልጸዋል፡፡

ድጋፉን የተረከቡት የኮሌጁ ዋና አዛዥ ሜጀር ጄነራል ሀብታሙ ጥላሁን በአሸባሪው ሕወሓት እየወደመ ያለውን የሀገር ሀብት እና ዜጎች ላይ የደረሰውን አሰቃቂ ጥቃት ለመመከት ሰራዊቱ ከፍተኛ ወኔ ላይ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡

በትዝታ ወንድሙ