የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ማዕከላዊ ኮሚቴ እየተወያየ ይገኛል

ግንቦት 8/2014 (ዋልታ) የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ማዕከላዊ ኮሚቴ በሊጉ የ1ኛ ዓመት ጉባኤ ዝግጅት ላይ እየመከረ ነው፡፡

የፓርቲው ሴቶች ሊግ የብልፅግና ፓርቲ ባካሄደው 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ያስቀመጣቸውን አቅጣጫዎች መገምገሙ ተገልጿል።

ፓርቲው በየዘርፉ ያስቀመጣቸውን አቅጣጫዎች እና እቅዶች እንዴት ተተገበሩ የሚለውን ክትትል ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነም ተመላክቷል።

የሊጉ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ትላንት ባደረጉት ግምገማ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እና የኑሮ ውድነትን መገምገማቸው ነው የተገለፀው።

ምግቤን ከጓሮዬ ጤናዬን ከምግቤ በሚል መሪ ሀሳብ የተጀመረው ንቅናቄ ተጠናክሮ መቀጠሉን በግምገማው ማየት መቻሉ ተገልጿል፡፡

በከተማ የግብርና እና በክልሎች  የዘር አቅርቦት ችግር እንዳለ የተገለፀ ሲሆን ሴቶችን ደግፎ ይበልጥ ለውጤት ማብቃት አስፈላጊ እንደሆነ ግምገማ መደረጉም ተጠቅሷል።

በሱራፌል መንግስቴ