የብልጽግና ፓርቲ አንደኛ ድርጅታዊ ጠቅላላ ጉባኤ እየተካሄደ ነው

የብልጽግና ፓርቲ 1ኛ ጉባኤ

መጋቢት 2/2014 (ዋልታ) የብልጽግና ፓርቲ አንደኛ ድርጅታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ከፈተና ወደ ልዕልና በሚል መሪ ዓላማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ጉባኤው ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጨት በጀመረበት ማግስት መካሄዱ ልዩ እንደሚያደርገው ተጠቁሟል፡፡

ጉባዔው ከዛሬ ጀምሮ እስከ መጋቢት 4/2014 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ችግሮች መፍታት ላይ ያተኮሩ ውሳኔዎች ይተላለፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW