የብሔራዊ ባንክ ሠራተኞች ከ19 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ

መስከረም 4/2015 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሠራተኞችና አመራሮች ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ድጋፍ የሚውል የአንድ ወር ደመወዛቸውን ከ19 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ፡፡

የባንኩ ሠራተኞችና የአመራር አባላት በቀጣዩ ሣምንት ደም ለመለገስ ፕሮግራም መያዛቸውንም ባንኩን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል፡፡