የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ በዲግሪ መርሃግብር ያስተማራቸውን 827 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በአራት ኮሌጆች በ14 የትምህርት ክፍሎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎችን ነው እያስመረቀ የሚገኘው፡፡
ከተመራቂዎቹ መካከል 508 ወንዶች ሲሆኑ፣ ቀሪዎች ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡
በምርቃት መርኃግብሩ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዱ፣ የዩኒቨርሲቲ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ በልጅጌን ጨምሮ የክልልና የፌደሬራል ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
ከአራተኛ ትውልድ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መካከል አንዱ የሆነውና እ.ኤ.አ በ2030 በተፈጥሮ ሀብት አስተዳደርና አጠቃቀም ከአፍሪካ ካሉት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ቀዳሚው ለመሆን አቅዶ እየሰራ የሚገኘው ዩኒቨርሲቲው በ2010 ዓ.ም ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር የጀመረ ሲሆን፣ በአሁኑ ሰአት በቀንና በማታ መርሃግብሮች 6 ሺ 348 ተማሪዎችን በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡
(በአለበል አለማየሁ)