ኅዳር 28/2014 (ዋልታ) የጉምሩክ ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ አንጋፋ አትሌቶች ማኅበርና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ለአገር መከላከያ ሰራዊት ከ98 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽን 20 ሚሊዮን ጥሬ ገንዘብ እንዲሁም 8 ሚሊዮን ብር የሚገመት የዓይነት ድጋፍ አድርጓል፡፡
የኢትዮጵያ አንጋፋ አትሌቶች ማኅበር ከ100 ሺሕ ብር በላይ ግምት ያለው የዓይነት ድጋፍ ያደረገ ሲሆን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ከ70 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ በዛሬው እለት አድርገዋል፡፡
ኢትዮጵያውያን አሸባሪውን ሕወሓት በማስወገድ አገርን ከጥፋት ለመታደግ በሚደረገው ርብርብ ድልን እየተቀዳጀች ትገኛለች ያሉት የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዊጂ እያገኘን ላለነው ድልም ለመከላከያ ሰራዊት ሲደረጉ የቆዩ ድጋፎች አስተዋጽዖ አላቸው ብለዋል::
ድጋፎች አሁንም ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል::
በሔብሮን ዋልታው