የተረጋጋ ማክሮኢኮኖሚ ለስራ አጥነት እና ኑሮ ውድነት

ጥቅምት 12/2014 (ዋልታ) በኢትዮጵያ የተረጋጋ ማክሮኢኮኖሚ በመፍጠር የስራ አጥነት እና የኑሮ ውድነት ችግርን ለማቃለል እንደሚሰራ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ተናገሩ።
የስራና ክህሎት ሚኒስቴር አመራሮች እና ሰራተኞች በቀጣይ በሚያከናውኑት ስራ ላይ ያተኮረ ውይይት አድርገዋል፡፡
በመርኃግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የስራና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል “በኢትዮጵያ የተረጋጋ ማክሮኢኮኖሚ በመፍጠር የስራ አጥነት እና የኑሮ ውድነት ችግርን ለማቃለል በትኩረት ይሰራል” ብለዋል።
በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና ፖለቲካዊ መስኮች ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት እንደሚሰራ አመልክተው፤ በተለይም የስራ አጥነት ችግርን ለማቃለል እንደሚሰራ ጠቅሰዋል።
“ዜጎች ባላቸው ክህሎት በየትኛውም የአገሪቱ አካባቢ በመሰማራት ውጤታማ ስራ እንዲያከናውኑ ይደረጋል” ያሉት ሚኒስትሯ፤ በኢትዮጵያ በእውቀትና ክህሎት ተወዳዳሪ እንዲሁም ምርታማ የሰው ኃይል መፍጠር ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫ እንደሚሆን አመልክተዋል።
በሰለሞን በየነ
ፈጣን መረጃዎች