የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ የወሰደውን የተኩስ አቁም ውሳኔ እንደምትደግፍ ገለጸች

ሰኔ 23/2013 (ዋልታ) – የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ የወሰደውን የተኩስ አቁም ውሳኔ እንደምትደግፍ ገልጻለች።

የኢትዮጵያ መንግስት ውሳኔ በሀገሪቱ ውስጥ ሰላም፣ መረጋጋትና ብልጽግና እንዲሰፍን አስተዋጽኦ እንዳለው የአገሪቱ የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር ያወጣው መግለጫ ያመለክታል።