የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ዋንጫ ሽኝት ስነስርዓት በዱከም እየተካሄደ ነዉ

ነሐሴ 19/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዋንጫ ሽኝት ሰነስርዓት በዱከም ከተማ እየተካሄደ ነዉ።

ከከተማው ነዋሪዎች፣ ከባለሀብቶች እንዲሁም ከተለያዩ አካላት በቦንድ ግዢ እና በስጦታ ከ19 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን የዱካም ከተማ ከንቲባ አብዱልጀቢል አብድሮ ተናግረዋል ።

በከተማዉ ከዚህ ቀደም ለግድቡ የተለያየ  ድጋፍ ሲደረግ መቆየቱን አንስተዉ ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አወሉ አብዲ በበኩላቸው በክልሉ የተለያዩ የልማት ስራዎች እየተሰሩ  መሆኑን ተናግረው  የክልሉ ህዝብ እና መንግስት ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር  በመሆን ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አሁን ያለበት ደረጃ ማድረስ መቻሉን ገልጸዋል።

የዱካም ከተማ ነዋሪዎችም  ግድቡ ሶስተኛ ዙር ሙሌቱን ባጠናቀቀበት ማግስት  ለግደቡ ይህን ያህል ገቢ ማሰባሰቡ የሚደነቅ መሆኑን የተናገሩት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ የኢትዮጵያ ህዝብ ለግድቡ መጠናቀቅ የሚያደረገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

ፌናን ንጉሴ (ከዱከም)