የታላቁ አሊምና ፈቂህ ሐጅ ሙሐመድ አልሳፊ ህልፈት

መስከረም 2/2014 (ዋልታ) ታላቁ አሊምና ፈቂህ ሐጅ ሙሐመድ አልሳፊ ማረፋቸውን የኢትየጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ገለፀ፡፡

ሼሕ ሙሐመድ አልሳፊ ከሐጅ ሙሐመድ ሳኒ ሀቢብ ጋር በመሆን በኢትዮጵያ መጅሊስን በመመስረትና የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሊቀመንበር በመሆን አገልግለዋል፡፡

ለእምነታቸው ባላቸው ቀናኢነት የተነሳ በደርግ መንግሥት ታስረው ከፍተኛ የሆነ ግርፋትና ድብደባ የተፈፀመባቸውና በዚህም ምክንያት የመናገር ልሳናቸው ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደርሶባቸው አባት ናቸው፡፡

የቀብር ሥነ ስርዓታቸው ትላልቅ መሻኢኾች በተገኙበት ዛሬ መስከረም 2 ኮልፌ በሚገኘው የእስልምና አማኞች መቃብር እንደሚፈጸም ከኢትየጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ዋልታ ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን ይመኛል፡፡