የትምህርት ሚኒስትሩ በሐረሪ ክልል የትምህርት ዝግጅት ስራዎችን እየጎበኙ ነው

ነሐሴ 26/2014 (ዋልታ) የኢፌዴሪ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በሐረሪ ክልል እየተከናወኑ የሚገኙ የትምህርት ዝግጅት ስራዎችን እየጎበኙ ይገኛል።

ሚኒስትሩ በሐረር ከተማ በሚገኘው መንፈሳዊ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት ከመማር ማስተማሩ አቅጣጫ ጋር በተያያዘ የመማርያ ክፍል ዝግጅቶችን ተመልክተዋል።

እንዲሁም በሐረር አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተማሪዎችን ለማብቃት እየተሰጠ የሚገኘውን የማጠናከርያ ትምህርት ስራ ገብኝተዋል።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ በምልከታቸው በሐረር ከተማ የሚገኘውን የሃረማያ ዩኒቨርሲቲ የጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅን እና የህይወት ፋና ስፔሻላይዝድ ቲቺንግ ሆስፒታልን የስራ እንቅስቃሴ ይመለከታሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ጎን ለጎንም በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ በመገኘት ከመምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች ጋር እንደሚወያዩ የኢዜአ ዘገባ አመልክቷል።