የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተደዳር ከመንግስት ሰራተኞች ጋር ተወያየ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በመቀሌ ከተማ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ወደ መደበኛ ስራቸው መመለሳቸውን በማስመልከት ውይይት አካሄደ፡፡

በውይይቱም በመቀሌ ከተማ በሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ሲሰሩ የነበሩ በርካታ ሰራተኞች ተሳትፈዋል፡፡

ሰራተኞቹም የህግ ማስከበር ዘመቻው በተካሄደበት ወቅት ከአንድ ወር በላይ በቤታቸው መቆየታቸውን ተናግረዋል፡፡

ሰራተኞቹ ‘የመንግስት ሰራተኛ የህዝብ አገልጋይ እንጂ የፖለቲካ አራማጅ አይደለም’ ያሉ ሲሆን፤ ወደ መደበኛ ስራቸው ለመመለስም ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በመቀሌ ከተማ የሚገኘው ሰላም ስራቸውን በአግባቡ ለመስራት የሚያስችል በመሆኑ ህዝብ የማገልግል ስራቸውን ለመጀመር ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል ሲል የዘገበዉ ኢዜአ ነዉ፡፡