የቻይናና ኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ዘርፍ ትስስር ለማጠናከር ይሰራል

መጋቢት 26/2014 (ዋልታ) ቻይና እና ኢትዮጵያ በኢንዱስትሪው ዘርፍ ያላቸውን ትስስር ለማጠናከር እንደሚሰራ በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ አስታወቀ።

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዛሆ ጂአኑሃ በአማራ፣ ሲዳማና ደቡብ ክልሎች እንዲሁም በድሬዳዋ የሚገኙ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ጎብኝተዋል።

ኤምባሲው የአምባሳደሩን ጉብኝት አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ የቻይናና ኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ዘርፍ ትስስር ለማጠናከር የሚያስችሉ ተግባራት ይከናወናሉ ብሏል።

ዘርፉን ለማጠናከር የሚከናወነው ሥራ የሁለቱን አገራት ተጠቃሚነት እንደሚያጎለብተውና ዘርፈ ብዙ የሥራ እድል እንደሚፈጥር አመልክቷል።

ቻይናና ኢትዮጵያ በኢንዱስትሪው ዘርፍ ባለሃብቶችን ከማሰማራት አንስቶ በቴክኖሎጂና ገበያ ትስስር እንዲሁም በሰው ኃይል አቅም ግንባታ የሁለትዮሽ ተግባራትን እንደሚያከናውኑ ይታወቃል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW