የ’ኃይሌ ሪዞርት’ 11ኛው ቅርንጫፍ በወልቂጤ ሊገነባ ነው

ጥር 29/2014 (ዋልታ) አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የ’ኃይሌ ሪዞርት’ ቅርንጫፍ በወልቂጤ ከተማ ለመገንባት የሚያስችለው የመሰረት ድንጋይ አስቀመጠ፡፡
ፕሮጀክቱ 500 ሚሊዮን ብር እንደሚፈጅም ተገምቷል፡፡
የወልቂጤ ከተማ በቀን በአማካይ ከ52 ሺሕ በላይ መንገደኞች የሚያልፍባት የንግድ ከተማ መሆኗን ተከትሎ የሆቴሉ በአካባቢው መገንባት የምጣኔ ሃብት መነቃቃትን ይፈጥራል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል።
አትሌት ሻለቃ ኃይሌ በዞኑም ሆነ በክልሉ ለሚያካሂዳቸው የኢንቨስተመን ሥራዎች የክልሉ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ርስቱ ይርዳው ተናግረዋል።
የሆቴል ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ ለበርካታ የግል ባላሃብቶች ፈቃድ መሰጠቱን ያነሱት ርዕሰ መስተዳድሩ ፈቃድ የወሰዱ ባለሃብቶች ወደ ሥራ እንዲገቡና አካባቢያቸውን እንዲያለሙ ጠይቀዋል።
በተጨማሪም የየአካባቢው ነዋሪዎች ወደ ስፍራው የሚመጡ የኢንቨስመንት እድሎችን መደገፍ እንዳለባቸው መልክታቸውን አስተላልፈዋል።
የፕሮጀክቱ ግንባታ እስኪጠናቀቅ በቀጥታ የሚከታተሉትም ርዕሰ መስተዳድሩ መሆናቸው ተገልጿል።
ሚልኪያስ አዱኛ (ከወልቂጤ)