የአማራና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ርዕሰ መስተዳድሮች በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ተወያዩ

የካቲት 2/2014 (ዋልታ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አቻቸው አሻዲሊ ሀሰን በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ተወያዩ።

ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል በሁለቱ ክልሎች የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር የተጀመሩ የውይይት መድረኮችን ማስቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል።

የሰላምና የጸጥታ ሥራዎችን አጠናክሮ በመስራት ለሕዝቦች የሰላምና የልማት ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ትኩረት መስጠት እንደሚገባም ነው ርዕሰ መስተዳድረ ይልቃል የገለፁት።

ርዕሰ መስተዳደር አሻድሊ በበኩላቸው የሁለቱን ክልል ሕዝቦች ለዘመናት የቆየውን ወንድማማችነትና አብሮነት ይበልጥ በማጠናከር የጋራ ሰላምና የልማት ጠቃሚነትን ለማጎልበት እንደሚሰራም ገልጸዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ አያይዘው እንደ አገር ብሎም እንደ ክልል የገጠሙንን ፈተናዎች ተቀራርቦ በመስራት ችግሮችን በአሸናፊነት ልንወጣ ይገባል ማለታቸውን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።