የአሜሪካ ም/ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ ታይዋን ገቡ

ሐምሌ 26/2014 (ዋልታ) የአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ ታይዋን ገቡ፡፡

የፔሎሲ ጉብኝት ከባድ ዲፕሎማሲያዊ ራስ ምታትን በአሜሪካ መንግሥት ውስጥ መፍጠሩ እየተነገረ ነው።

የፔሎሲን የታይዋን ጉብኝት አስመልክቶ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የአፈ ጉባኤዋን ጉብኝት በጥብቅ አውግዟል፡፡

ከዛሬ ጀምሮም በታይዋን አቅራቢያ ተከታታይ ወታደራዊ ዘመቻ እንደሚያካሂድ አስታውቋል።

የታይዋን መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ በደሴቲቱ አቅራቢያ የሚካሄዱ የትኛውንም አይነት ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን እየተከታተለ መሆኑን እና ከቻይና የሚመጣን ማንኛውንም ስጋት ለመመከት ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።