የአሜሪካ “ብላክ ኮከስ” አባላት የህዳሴው ግድብ ድርድር የጋራ ተጠቃሚነትን ባከበረ መንገድ እንዲካሄድ ጠየቁ

የአሜሪካ “ብላክ ኮከስ” አባላት

ሰኔ 17/2013(ዋልታ) – ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት በማድረግ ድርድር እንዲካሄድ የአሜሪካ ኮንግረስ “ብላክ ኮከስ” አባላት ጠየቁ።

በግድቡ ጉዳይ ላይ ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ አሁንም የጋራ ተጠቃሚነትን እና ትብብር መሰረት ያደረገ ሰላማዊ ድርድር ሊያደርጉ ይገባል ብሏል።

ይህም ድርድር የጋራ ተጠቃሚነትን እና ዓለም አቀፍ ህጎችን ያከበረ ሊሆን ይገባል ነው ያሉት አባላቱ።

ግድቡ በአህጉሩ ትልቁ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ በመሆኑ ኤሌክትሪክ ለጎረቤት ሀገራት በመላክ መልካም አጋጣሚ ሊሆን እንደሚችልም ጠቁመዋል።

የ“ብላክ ኮከስ” አባላቱ አሜሪካ እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ተዋንያን በአውሮፓውያኑ 2015 ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ የፈረሙትን የሶስትዮሽ ድርድር ሊያከብሩ ይገባል ብሏል።

አሜሪካ እና ዓለም አቀፍ ተቋማት የህዳሴ ግድቡን በተመለከተ የአፍሪካ ህብረትን በማማከር ጠቃሚ ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ሁሉም ወገኖች ተጠቃሚ የሚሆኑበት ሰላማዊ ድርድር እንዲካሄድ የአፍሪካ ህብረት ወሳኝ ሚና አለውም ብሏል።

የአሜሪካ ኮንግረስ “ብላክ ኮከስ” አባላት የህዳሴው ግድብ ለአህጉሩ ካለው ፋይዳ አንጻር እንዲጠናቀቅ ሰላማዊ ድርድርን እንደሚደግፉ አስታውቀዋል።