የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት በትግራይ ክልል ከ1 ሚሊዮን በላይ ለሚበልጡ ዜጎች የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ማድረጉን ገለጸ

መጋቢት 3/2013 ዓም (ዋልታ) – የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት(ዬኤስ ኤድ) ከካቶሊክ የእርዳታ አገልግሎት ጋር በመሆን በትግራይ ክልል ከ1 ሚሊዮን ለሚበልጡ ዜጎች የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ማድረጉን ገልጿል።

የተራድኦ ድርጅቱ ከህዳር ወር ጀምሮ እስካሁን 34 ሺ ሜትሪክ ቶን የአስቸኳይ ጊዜ ምግብ ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል፡፡

የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅትና የካቶሊክ እርዳታ አገልግሎት በትግራይ ክልል ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ተጨማሪ ድጋፍ ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉ ማስታወቃቸውን ዩኤስ ኤድ ኢትዮጵያን ዋቢ አድርጎ ኢዜአ ዘግቧል ፡፡