የአሜሪካ ኤምባሲ ከሽብር ፈጣሪ መግለጫዎቹ እንዲቆጠብ መንግሥት አሳሰበ

ኅዳር 16/2014 (ዋልታ) የተለያዩ አገራት ኤምባሲዎች ዜጎቻቸውን ለማውጣት ያደረጉት ሙከራ ስህተት መሆኑ ሲገባቸው ሀሳባቸውን እየቀየሩ ነው ሲል መንግሥት አስታወቀ፡፡

በዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብ የኢትዮጵያን ስም ለማጠልሸት የሚደረገው ሙከራ ፍጹም ስህተት መሆኑ ተገልጿል፡፡

የአሜሪካ ኤምባሲ እንደዚህ ዓይነት መግለጫ ከማውጣት እንዲቆጠብ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ደሲሳ አሳስበዋል፡፡

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት በአዲስ አበባ የሚገኙ ኤምባሲዎችን የማስፈራራት ስራ ከመስራት እንዲቆጠቡም በሰጠው መግለጫ አስጠንቅቋል፡፡