የአሜሪካ ኮንግረስ አባል ጆን ጋራምዲ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለመገንባት ኮንግረሱ መንግሥትን መደገፍ አለበት አሉ

የአሜሪካ ኮንግረስ አባል ጆን ጋራምዲ

ሚያዝያ 19/2014 (ዋልታ) የአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ጆን ጋራምዲ የአሜሪካ ኮንግረስ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለመገንባት በምርጫ ሥልጣን የያዘውን መንግሥት መደገፍ አለበት አሉ፡፡

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ ለኢትዮጵያ ጊዜ የማይለውጠው ድጋፍ እያደረጉ ነው ያሏቸውን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ጆን ጋራምዲ አመስግነዋል፡፡

አምባሳደሩ በኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ ከተመራው ልዑክ ጋር ሆነው ከካሊፎርኒያ ግዛት የኮንግረስ አባል ጋራምዲ ጋር ያደረጉትን ውይይት በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አያይዘው ባወጡበት ተንቀሳቃሽ ምስል ነው ምስጋናቸውን ያቀረቡት፡፡

የምክር ቤቱ አባል በአፍሪካ ቀንድ የምንጋራውን የጋራ ፍላጎት፣ ሰላምና ብልጽግና በወጉ የሚረዱ ናቸው ብለዋል፡፡

አምባሳደር ፍፁም አክለውም በዚህም ዓስርት ዓመታትን በኢትዮጵያ በጎና ክፉ ጊዜ ሳይናወጥ ለዘለቀው ድጋፋቸው ኮንግረስ ማን ጆን ጋራምዲን እናደንቃለን ሲሉ ጽፈዋል፡፡

የምክር ቤት አባሉ በበኩላቸው የአሜሪካ ኮንግረስ ወይም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለመገንባት በምርጫ ሥልጣን የያዘውን መንግሥት መደገፍ አለበት ብለዋል፡፡

 

ለፈጣን መረጃዎች፦

ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!