የአሜሪካ ዩኤስኤይድ ኃላፊ ሳማንታ ፓዎር የአሸባሪው ሕወሓትን የነደጅ ዝርፊያ አወገዙ

ሳማንታ ፓዎር

ነሐሴ 20/2014 (ዋልታ) የአሜሪካ የልማት ተራድኦ ድርጅት /ዩኤስኤይድ/ ኃላፊ ሳማንታ ፓዎር አሸባሪው ሕወሓት በመቐለ የተባበሩት መንግሥታት የዓለም ምግብ ፕሮግራም ነደጅ መዝረፉን በፅኑ እንደሚያወግዙ አስታውቀዋል፡፡

ከዘረፋው ባሻገር የረድኤት ድርጅት ሰራተኞቹ ላይ የደረሰው ወከባ እና ማስፈራሪያ ተቀባይነት እንደሌለውም አመልክተዋል፡፡

ችግር ላይ ያሉ ኢትዮጵያዊያንን ለመመገብ የሚደረገውን ጥረት ቡድኑ 570 ሺሕ ሊትር (150ሺ ጋሎን) ነዳጅ በመዝረፍ ማስተጓጎሉ የጨካኝነት ጥግ ማሳያ መሆኑን ሳማንታ ፓዎር በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

አሸባሪው የሕወሓት ቡድን የዘረፈውን ነዳጅ እንዲመልስ እና የሰብአዊ እርዳታ ሥራን እንዲያከብርም ኃላፊዋ አሳስበዋል፡፡

 

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!