የአርቲስት ዓሊ ቢራ አስክሬን ቢሾፍቱ ከሚገኘዉ የአርቲስቱ ቤት ሽኝት እየተደረገለት ነው

የአርቲስት ዓሊ ቢራ አስክሬን ሽኝት

ጥቅምት 29/2015 (ዋልታ) የአርቲስት ዓሊ ቢራ አስክሬን ቢሾፍቱ ከሚገኘው የአርቲስቱ ቤት ሽኝት እየተደረገለት ነው፡፡

ዛሬ ለአንጋፋው አርቲስት ክብር ዶ/ር ዓሊ ቢራ የጀግና የክብር ሽኝት እና ሥርዓተ ቀብር ይፈጸማል፡፡

የቀብር አስፈጻሚው ኮሚቴ እንደገለጸው አስክሬኑ ቢሾፍቱ ከሚገኘው የአርቲስት ዓሊ ቢራ መኖሪያ ቤት ወደ ወዳጅነት አደባባይ የሚመጣ ሶሆን የአሸኛኘት ፕሮግራሙ በወዳጅነት አደባባይ ከ3፡00 ጀምሮ በተለያዩ ሥነ ሥርዓቶች ይከናወናል፡፡

በወዳጅነት አደባባይ የክብር እና የጀግና ስንብት ከተደረገለት በኋላም ወደ ድሬዳዋ አስክሬኑ እንደሚሸኝም ነው የተገለጸው።

ድምጻዊ ዓሊ ቢራ በአዳማ አጠቃላይ ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በ75 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ይታወሳል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW