የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ አዲስ መመሪያ አስተላለፈ

ኅዳር 20/2014 (ዋልታ) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ከአምራች ኢንዱስትሪዎች ጋር በተያያዘ አዲስ መመሪያ አስተላልፏል፡፡
ዕዙ አሁን ባለው አገር የማዳን ግዳጅ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን አስታውሷል፡፡
በዚህ ምክንያትም በአንዳንድ አካባቢዎች የሰዓት እላፊ ገደብ የተደረገ ቢሆንም በአምራች ኢንዱስትሪዎች ላይ ገደቡን ተግባራዊ ማድረግ ከፍተኛ የሆነ የምጣኔሃብት ጫና ስለሚያሳድርና ኢንዱስትሪዎችንም ወደ ኪሳራ ስለሚያስገባቸው የተቀመጠው የሰዓት እላፊ ገደብ ለሁሉም አምራች ኢንዱስትሪዎች እንደማይመለከት አስታውቋል፡፡
በመሆኑም ኢንዱስትሪዎቹ አስፈላጊ የሆነ የራሳቸውን የጥበቃ ስርዓት ከወትሮው በተለየ መልኩ አጠናክረው መደበኛ ሥራቸውን በተለመደው ሁኔታ እንዲቀጥሉ እንዲደረግ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡