የአሸባሪው ሕወሓት ታጣቂዎች በነፋስ መውጫ ከተማ የአስገድዶ መድፈር ጥቃቶች መፈጸማቸውን አምነስቲ አመለከተ

አምነስቲ ኢንተርናሽናል

ኅዳር 1/2014 (ዋልታ) አምነስቲ ኢንተርናሽናል የሕወሓት ታጣቂዎች በአማራ ክልል የነፋስ መውጫ ከተማ ላይ ጥቃት በፈጸሙበት ጊዜ ከአስገድዶ መድፈር፣ ዘረፋ እና አካላዊ ጥቃቶች በተጨማሪ አዋራጅ ንግግር ሲናገሩ እንደነበር ሪፖርት አድርጓል።

አስገድዶ መደፈረ የተፈፀመባቸው ሁሉም ሴቶች ፈጻሚዎቹ ሕወሓቶች መሆናቸውን መለየት የቻሉት በአነጋገር ዘያቸው እና በሚሰነዝሩት ብሔርን መሠረት ባደረገ ስድብ እንዲሁም ደግሞ በግልጽ ሕወሓቶች መሆናቸውን በመናገራቸው መሆኑን ለአምነስቲ ኢንተርናሽናል ተናግረዋል።

ታጣቂዎች በሴቶቹ ላይ የአስገድዶ መድፈር ከመፈፀማቸው በተጨማሪ ሰብዓዊነትን የሚያጣጥል የብሔር ማንነታቸው ላይ ያነጣጠሩ ስድቦችንና ማዋረድን ይፈጽሙ እንደነበርም የአምነስቲ ሪፖርት አመላክቷል።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው ሪፖርት ላይ እንዳመለከተው በከተማዋ ነዋሪ የሆኑና ያናገራቸው 16 ሴቶች በአሸባሪው ሕወሓት ታጣቂዎች የአስገድዶ መደፈር ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል።

አንድ ለአምነስቲ ሪፖርት ያደረጉ የክልሉ ባለሥልጣን ለአምነስቲ እንደገለጹት ደግሞ የአሸባሪ ቡድኑ በንፋስ መውጫ ከተማ ከ70 በላይ ሴቶችን መድፈራቸው ሪፖርት አድርገዋል።

የፌደራል ፍትህ ሚኒስቴር መረጃ ደግሞ አሃዙ 73 እንደሆነ ያመለክታል፡፡