የአሸባሪውን የህወሐት ቡድን ለመደምሰስ ዝግጁ መሆናቸውን የፓለቲካ ፓርቲዎች ገለፁ


ሐምሌ 27/2013 (ዋልታ) –
የአሸባሪውን የህወሐት ቡድንን ለመደምሰስ ማንኛውንም አይነት መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን የፓለቲካ ፓርቲዎች ገለፁ።
አምስት የፓለቲካ ፓርቲ ድርጅቶች በሰጡት የጋራ መግለጫ ሽፍታው የህወሐት ቡድን ለመደምሰስ ማንኛውንም አይነት መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን አስታወቁ።
የጋራ መግለጫ የሰጡት አዲስ ትውልድ ፓርቲ፤ ህዳሴ ፓርቲ፤ ራያራዩማ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ፤ የኢትዮጵያ ነፃነት ፓርቲ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ ናቸው።
ፓርቲዎቹ በጋራ መግለጫቸው እንዳስታወቁት አሸባሪው የህወሐት ቡድን የትግራይን ህዝብ እንደመሸሸጊያ ተጠቅሞ የፌደራሉ መንግስት የወሰደውን የተናጠል የተኩስ ውሳኔ ወደ ኋላ በመተው በሶስት አቅጣጫ መጠነ ሰፊ ውጊያ ከፍቶብናል ብለዋል።
ይህንንም ውጊያ ህፃናት፤ ሴቶችና አረጋውያንን ከፊት አሰልፎ፤ ለዓለም አቀፍ ድንጋጌዎችንም ባለመገዛት ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎችን በአደንዛዥ እፅ በመጠቀም በጦርነት እየማገደ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
አሸባሪው ህወሐት ህዝቡን እንደጋሻ መሸሸጊያ መጠቀሙ ምን ያህል ለትግራይ ህዝብ እንኳን ዴንታ የሌለው መሆኑ የሚያሳይ ፀረ ህዝብና ፀረ ሀገር በመሆኑ የፓርቲዎቻችን አመራሮችና አባሎች በአውደ ውጊያ ግንባር በመዝመት ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጋር ሆነን ወራሪውን የሽብር ቡድን ለመመከትና ለማጥፈት ዝግጁ ነን በማለት ገልፀዋል።
(በደረሰ አማራ)