የአባቶቻችንን የጀግንነት መንፈስ ተላብሰን ወደ ግንባር በመትመም የአሸናፊነት ታሪካችንን ልናስቀጥል ይገባል – የአማራ ብልፅግና ፓርቲ

ኅዳር 14/2014 (ዋልታ) ወደ ግንባር ለሚዘምቱ በአማራ ክልል የሚገኙ የመንግስትና የልማት ድርጅት ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች የሽኝት መርኃግብር እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ ፅሁፍ ያቀረቡት በአማራ ብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ፍስሀ ደሳለኝ ጊዜው ህይወትን እስከመስጠት በደረሰ ቁርጠኝነት ኅልውናችንን ለማስከበር ወደ ግንባር የምንዘምትበት፣ በአንድ ቆመን ጠላትን በመደምሰስ በወራሪ ቡድኑ መቃብር ላይ ኢትዮጵያን የምናፀናበት ነው ብለዋል።

የአባቶቻችንን የጀግንነት መንፈስ ተላብሰን ወደ ግንባር በመትመም የአሸናፊነት ታሪካችንን ልናስቀጥል ይገባልም ሲሉም አክለዋል።

በመርኃግብሩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) እና በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማእረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ ስዩም መኮንንና ሌሎችም የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን ኢብኮ ዘግቧል።