የአብነት መንፈሳዊ ት/ቤት እጩ መምህራንና ተማሪዎች ምረቃ እየተካሄደ ይገኛል

ግንቦት 14/2013 (ዋልታ) – በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን የዳግማዊ ሚኒሊክ መታሰቢያ መምህራንና ቀሳውስት ማሰልጠኛ የአብነት መንፈሳዊ ት/ቤት እጩ መምህራንና ተማሪዎቹን እያስመረቀ ይገኛል ።

መንፈሳዊ ት/ቤቱ በአጠቃላይ በአጫጭር የስብከት ትምህርት መስክ ለሁለት አመታት ስልጠና የወሰዱና በእጩ መምህራንነት ደግሞ ለአምስት አመታት ትምህርታቸውን የተከታተሉ 170 ተማሪዎችን ነው በማስመረቅ ሂደት ላይ የሚገኘው።

እጩ መምህራኑ በአዲስ ኪዳን፣ በብሉይ ኪዳን፣ በመፅሀፈ ሊቃውንት በቅኔ ላይ ትኩረት አድርገው ስልጠናቸውን ተከታትለዋል ተብሏል።

ተመራቂ ተማሪዎቹ በመንፈሳዊ ት/ቤቱ ያገኙትን እውቀት ትውልድ ለማነፅና መልካም ዜጋ እንዲፈጠር ለማድረግ እንደሚሰሩበት ገልፀዋል።
(በሱራፌል መንግስቴ )