የአብን ምክትል ሊቀመንበር የሱፍ ኢብራሂም ቃለ መሃላ ፈጸሙ

የአብን ምክትል ሊቀመንበር የሱፍ ኢብራሂም

ጥቅምት 10/2014 (ዋልታ) በቅርቡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት የሱፍ ኢብራሂም ቃለ መሃላ ፈጸሙ፡፡

የአስተዳደሩ ምክር ቤት በቅርቡ ባካሄደው መስራች ጉባኤ በከንቲባ አዳነች አቤቤ አቅራቢነት የአዲስ አበባ ከተማ የመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው  የተሾሙት የአብን ምክትል ሊቀመንበር የሱፍ ኢብራሂም የአዲስ አበባ ከተማ አፈ ጉባኤ ቡዜና አልከድር በተገኙበት በዛሬው ዕለት ቃለ መሃላ መፈጸማቸው ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።