የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ማስፋፊ ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት ደም ለገሱ

ነሀሴ 21/2013 (ዋልታ) – የፌዴራል አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ማስፋፊያ ባለስልጣን አመራርና ሰራተኞች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ደም ለግሰዋል፡፡
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አስፋው አበበ የባለስልጣኑ አመራርና ሰራተኞች ከዚህ ቀደም ከአንድ ሚሊዬን ብር በላይ የሚሆን የአንድ ወር ደመወዛቸውን ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልፀው ለመከላከያ ሰራዊቱ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
በዚህ ወቅት የሚደርሰውን የኢኮኖሚ ጫና ለመቀነስ ሁሉም በተሰማራበት የስራ መስክ ውጤታማ ስራ መስራት ይገባልም ብለዋል።
ደም የለገሱ የባለስልጣኑ ሰራተኞች እንደገለፁትህይወቱን ሰውቶ የሀገርን ሰላምና ሉኡላዊነት ለማስከበር በግንባር ላለው የመከላከያ ሰራዊት ያላቸውን አክብሮትና ደጀንነት በማረጋገጥ በሁሉም መልኩ ከጎኑ እንቆማለን ብለዋል።
የባለስልጣኑ አመራሮችና ሰራተኞች ሀገር ከገባችበት የህልውና አደጋ እስክትወጣ ድረስ በሁልም መስክ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የተናሩ ሲሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሀላፊነት መሆን ይገባል ሲሉም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
(በሳራ ስዩም)