ሰኔ 09/2013 (ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጅማ ከተማ የተገነባውን የአዌቱ የወንዝ ዳር ልማት ፕሮጀክት መርቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ተመስገን ጥሩነህ፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ፣ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ እና የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሠ ጋር በመሆን ነው ዛሬ ረፋድ ጅማ ከተማ የገቡት፡፡