ኅዳር 15/2014 (ዋልታ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የአስፈጻሚ አካላት ማቋቋሚያ ስልጣንና ተግባር አዋጅ አጸደቀ፡፡
በምክር ቤቱ ለተነሱ ጉዳዮች በክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተደድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ተጨማሪ ማብራሪያ ቀርቦ በምክር ቤቱ አባላት በሙሉ ድምጽ ጸድቋል።
የአስፈጻሚ አካላት መስሪያ ቤቶች የመስተዳድር ምክር ቤት አባል ሆነው በዚህ አዋጅ የተቋቋሙት እንደሚከተለው ቀርበዋል፡-
- ርዕሰ መስተዳድር
- ሠላምና ጸጥታ አስተዳደር
- ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት
- ግብርና ቢሮ
- ፍትህ ቢሮ
- ሴቶች፣ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ
- ትምህርት ቢሮ
- ጤና ቢሮ
- ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ
- ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ
- ባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ
- ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ
- የአርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢ ጉዳይ ቢሮ
- የገቢዎች ቢሮ
- ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ
- ክህሎትና ቴክኖሎጂ ቢሮ
- ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ
- መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
- ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሠው ሀብት ልማት ቢሮ
- ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ
- ደንና አካባቢ ጥበቃ ቢሮ
ከመስተዳድር ምክር ቤት አባላት ውጭ ያሉት አስፈጻሚ አካላት በዚህ አዋጅ የተቋቋሙ
- ግብርና ምርምር ኢንስቲዩት
- ቡና፣ሻይና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን
- ህብረት ሥራ ልማት ኤጀንሲ
- የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን
- መንገድ ባለስልጣን
- ከተማ ፕላን ኢንሰቲትዩት
- ኮንስትራክሽን ባለስልጣን
- ሚሊሻ ጽ/ቤት
- ፖሊስ ኮሚሽን
- የመንግስት ግዥ ኤጀንሲ
- ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን
- የማዕድንና ኢነርጂ ልማት ኤጀንሲ
- የመሥኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ
14.የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ
- ጤናና ጤና ነክ አገልግሎትና ግብዓት ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን
- የህብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት