የአዲስ አበባ የፀጥታ ሁኔታ አስተማማኝ ደረጃ ላይ መሆኑን ፖሊስ ገለፀ

ጥቅምት 27/2014 (ዋልታ) ከሰሞኑ በአዲስ አበባ ለሽብር ተግባር ሊውሉ የነበሩ የጦር መሳሪያዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉንና አሁን ላይ ፀጥታው አስተማማኝ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ዛሬ የአዲስ አበባን የሰላምና የፀጥታ ሁኔታ አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም ባለፋት ጥቂት ቀናት በሕብረተሠቡ ጥቆማና በተደረገ ክትትልና ፍተሻ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች አና የፖሊስ አልባሳት ተገኝተዋል ነው ያሉት።

ኮሚሽኑ በአሁኑ ወቅት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መመሪያን መሠረት በማድረግ የከተማዋን ፀጥታና ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ እየሠራ መሆኑን ገልፀዋል።

ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ እንዳመላከተው ኮሚሽነሩ በአሁኑ ወቅትም የከተማዋ ሰላም አስተማማኝ ደረጃ ላይ መሆኑን ገልጸዋል።