መስከረም 26/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ባለፉት ሁለት ወራት 10 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ገቢ በመሰብሰብ የዕቅዱን 119.8 በመቶ ማሳካተን አስታወቀ።
ባለፉት የሐምሌና በነሐሴ ወራት 8 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 10 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ገቢ በመሰብሰብ የዕቅዱን 119.8 በመቶ ማሳካት መቻሉ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ገልጿል፡፡
ቢሮው ገቢው ያሰባሰበው የደረጃ “ሀ”፣ “ለ” እና “ሐ” ግብር ከፋዮች እንደሆነ አንስቷል፡፡
ይኸው የግብር አሰባሰብ ስራ እስከ መስከረም መጨረሻ የታቀደው 11 ቢሊየን ብር ለማሰባሰብ ሲሆን ከቀሩን ጊዜያት አኳያ ቀሪዎቹን ለማሳካት ሰፊ ዕድል አለ ብሏል፡፡
ተቋሙ ስራው በቅልጥፍና እና እንግልት ባስወገደ አኳኋን እየሰራ ስለሆነ ግብር ከፋዮቻችን ግብር በወቅቱ በመክፈል የተለመደውን ሀገር ወዳድነት እና አጋርነት እንደሚያሳዩ እምነት እንዳለው ከአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡