የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በኮምቦልቻ ከተማ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገ

ኅዳር 30/2014 (ዋልታ) የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አመራሮችና ሰራተኞች በኮምቦልቻ ከተማ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አድርጓል።

ክፍለ ከተማው ኮምቦልቻ በመገኘት ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የአይነት ድጋፍ በወሎ ግንባር ለሚገኙ የኢትዮጵያ ጥምር ጦር አባላት ድጋፍ አድርገዋል።

ሠራተኞች፣ አመራሮችና ልዩ ልዩ አደረጃጀቶች ለሰራዊቱ የታሸጉ ምግቦችን ጨምሮ በሬዎችን በማበርከት የሰራዊቱ የኋላ ደጀንነታቸውን በተግባር ማረጋገጣቸውን ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።