የአዳማ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ መሰረተ ልማት ዙሪያ ከነዋሪዎች ጋር እየተወያየ ነው

 

የአዳማ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ በተሰሩ መሰረተ ልማቶች የስራ አፈፃፀም ላይ ከነዋሪዎች ጋር ውይይት እያደረገ ነው፡፡

የአዳማ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሀይሉ ጀልዴ መስተዳደሩ በርካታ የልማት ስራዎችን ለመስራት አቅዶ መንቀሳቀሱን ገልጸው፤ መንግስት ለህዝብ አገልጋይ በመሆኑ የተሰሩ ስራዎችን ጥንካሬና ድክመት ከህዝቡ ጋር ውይይት ማድረጉ አመርቂ ውጤት ለማምጣት በር ከፋች ነው ብለዋል፡፡

አዳማ ከተማን የብልፅግና ተምሳሌት ብሎም ምቹ እና እድገቷ የተፋጠነ ለማድረግ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን የተናገሩት ከንቲባው፣ ይህ የልማት ስራ ከከተማዋ እድገት ባለፈ ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድል የፈጠረ ነውም ብለዋል፡፡

በውይይት መድረኩም የአዳማ ከተማ ከንቲባ፣ አባገዳዎች እና የከተማው ነዋሪዎች እየተሳተፉ ነው፡፡
(በሄብሮን ዋልታው)