የአድዋ ድል በዓል በባህር ዳር ከተማ እየተከበረ ነው

የካቲት 23/2013 (ዋልታ) – 125ኛው ዓመት የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል በባህር ዳር ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት እየተከበረ ነው።

በበዓሉ አከባበር ሥነ-ሥርዓት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ከባህር ዳር ከተማ ስድስት ከፍለ ከተሞች የተውጣጡ ነዋሪዎች የአድዋን ገድል የሚያንጸባርቁ  የተለያዩ መፈክሮችን በማሰማት በዓሉ በሚከበርበት ስፍራ ታድመዋል።

“የአድዋ ድል ለአሁኑ ትውልድ የፍቅር፣ የፅናትና የአንድነት መሰረት ነው፣ በአድዋ የተገኘውን ድል ድህንትን በማጥፋት እንደግመዋለን እና  የአባቶቻችን ታሪክ የእኛም መሰረት ነው” የሚሉ  መፈክሮችን ነዋሪዎቹ አሰምተዋል፡፡

በበዓሉ አከባር የሃይማኖት አባቶች፣ ፈረሰኞችና ጦርና ጋሻ የያዙ አረበኞች የተገኙ ሲሆን፣ የተለያዩ  ትርኢቶች እየቀረቡ መሆናቸውን ከኢዜአ የተገኘው መረጃ አመላክቷል።