የአድዋና አክሱም ከተማ ነዋሪዎች የተጀመረውን ሰላም በማስቀጠል ወደ ልማት መግባት አስፈለጊ መሆኑን ገለጹ

ታኅሣሥ 18/2015 (ዋልታ) የአድዋ እና አክሱም ከተማ ነዋሪዎች የተጀመረውን ሰላም እና መረጋጋት በማስቀጠል ወደ ልማት መግባት አስፈለጊ መሆኑን ተናገሩ፡፡

በፌደራል መንግስትና በሕወሓት መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እየተመለሱ በሚገኙት የአድዋ እና አክሱም ከተሞች ከፌደራል መንግሥት የተወከሉ የሰላምና መረጋጋት ግብረ ኃይል አባላትና አመራሮች ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አካሂደዋል፡፡

በመድረኩ የከተማዋ ነዋሪዎች በተደረሰው የሰላም ስምምነት እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን በመግለፅ በህዝቡ ተሳትፎ የተጀመረውን ሰላም እና መረጋጋት በማስቀጠል ወደ ልማት መግባት አስፈለጊ መሆኑን አንስተዋል፡፡

መሰረተ ልማቶችን ዳግም ስራ ለማስጀመርና የሰብዓዊ እርዳታን ለማድረስ የተደረገውን ጥረት በማድነቅም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ሳሙኤል ሓጎስ (ከአድዋ)