የአገልጋይነት ክብር ቀን በአዲስ አበባ

የአገልጋይነት ክብር ቀን

ጳጉሜ 02/2013 (ዋልታ) ጳጉሜ 02 የአገልጋይነት ክብር ቀን በአዲስ አበባ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው፡፡

የአገልጋይነት ክብር ቀንን በማስመልከት በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የፅዳት ዘመቻ መርሐግብር በመከናወን ላይ ይገኛል።

ቀኑን አስመልከቶ የአዲስ አበባ  ምክትል ከንቲባ አዳነች አበቤ ባስተላለፉት መልዕክት ማገልገል ከምንም በላይ ክቡር የሆነ ተግባር ነው፤ አገልግሎት ሁሉ ሰው እድሜውን ሁሉ እየሰጠ እና እየተቀበለ የሚኖርበት የህይወት አካል ነው ብለዋል።

አገልጋይነት በእውነት ለገባው ትንሽ ትልቅ የማይባል፤ ከደሳሳ ቤት ጀምሮ እስከ ቤተ መንግስት አስቀድሞ ያለ፣ የነበረ፣ ወደፊትም የሚኖር ታላቅ ተግባር ሲሆን፣ መርሁም ታማኝነት፣ ቅንነት እና አክብሮት መሆኑንም ገልፀዋል።

በቀኑ የአገልጋይነት አስተምሮትና የአገልጋይነት ተምሳሌት ለሆኑ ለፀጥታ አካላት፣ የጽዳት ሰራተኞች፣ የእሳት አደጋ መከላከል ባለሙያዎች፣ ወጣት በጎ ፈቃደኞች፣ የመንግስት ሰራተኞች፣ የጤና ባለሙያዎች እና በተለያዩ ዘርፍ አገልግሎት የተሰማሩ የአመት በዓል ማዕድ ማጋራት እንዲሁም ስጦታ የመስጠት ስነ ሥርዓት እንደሚካሄድ የከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት መረጃ ያመለክታል፡፡