የአፋር ክልል ምክር ቤት የርዕሰ መስተዳድር እና አፈጉባኤዎች ሹመቶችን አጸደቀ

መስከረም 20/2014 (ዋልታ) የአፋር ክልል ምክር ቤት አቶ አወል አርባን ርዕሰ መስተዳድር አድጎ መረጠ፡፡

የአፋር ክልል ምክር ቤት ወ/ሮ አሲያ ከማልን አፈጉባኤ አድርጎ መርጧል፡፡

የክልሉ ምክር ቤት ዛሬ እያካሄደ ባለው 6ኛ የስራ ዘመን የመጀመሪያ የምስረታ ጉባኤው ወ/ሮ መይረም መሐመድን ምክትል አፈጉባኤ አድርጎ ሾሟል፡፡

አዲስ ተመራጮቹ ለህገ መንግሥቱ ታማኝ በመሆን ከክልሉ እና ከህዝቡ የተጣለባቸውን ሃላፊነት በቅንነትና በታታሪነት እንዲሁም ህግና ስርአትን መሠረት በማድረግ ስራቸውን እንደሚፈጽሙ ቃል ገብተዋል።