የአፍሪካ ኅብረት ሱዳንን ከአባልነት አገደ

ጥቅምት 17/2014 (ዋልታ) የአፍሪካ ኅብረት ሱዳንን ከአባልነት አገደ፡፡

ኅብረቱ ሱዳን በየትኞቹም የድርጊት መርሃ ግብሮቹ እንዳትሳተፍ ማገዱን አስታውቋል።

እገዳው የሽግግር ሂደቱን ይመራ የነበረው አስተዳደር ወደ ቦታው እስከሚመለስ የሚቀጥል ነውም ብሏል፡፡