የአፍሪካ ድንቃድንቆች መዝገብ ለዓለም አጭሯ ሴት እና የኢትዮጵያ ረጅሙ ወንድ እውቅና በመስጠት ሥራ ጀመረ

የአፍሪካ ድንቃድንቆች መዝገብ

መጋቢት 2/2014 (ዋልታ) በመጀመሪያው ዙር የአፍሪካ ድንቃድንቆች መዝገብ የዓለም አጭሯ ሴት የሻሌ ወርቁ ከወላይታ እና የኢትዮጵያ ረጅሙ ወንድ ነገዎ ጅማ ከመቂ እውቅና ተሰጣቸው፡፡

የዓለም አጭሯ ሴት ኢሻሌ ወርቁ 61 ሴ.ሜ ስትሆን የኢትዮጵያ ረጅሙ ወንድ ነገዎ ጅማ ደግሞ 2 ሜትር ከ25 ሴንቲ ሜትር መሆኑ ተገልጿል፡፡

በኢትዮጵያዊያን የተመሰረተው ይሄው የአፍሪካ ድንቃንቆች መዝገብ “ከምንም ወደ ታላቅንነት” በሚል መነሻነት የአገሪቷን ባህል በማስተዋወቅ እና ፈጠራን በማበረታታት ጀግኖችን መፍጠር ላይ ትኩረቱን በማድረግ ነው የመጀመሪያ ሥራውን እውቅና በመስጠት የጀመረው ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡