የኢትዮ ቴሌኮም የሰሜን ሰሜን ምዕራብ ሪጂን ስራተኞች ድጋፍ አደረጉ

ነሀሴ 21/ 2013 (ዋልታ) – የኢትዮ  ቴሌኮም የሰሜን  ሰሜን ምዕራብ  ሪጂን ስራተኞች  በማይጸብሪ ግንባር  ለሚገኘው ሠራዊት ግምቱ ከግማሽ  ሚሊዮን  ብር በላይ  የሆነ  የአይነት ድጋፍ  አደረጉ ።

ከተደረገው ድጋፉ ውስጥ  ምግብ  እና  አልባሳት  ይገኙበታል ።

የሪጅኑ ሰራተኞች  የህልውና  ትግሉ  በድል እስኪጠናቀቅ  ድረስ  ድጋፋቸውን  አጠናክረው እንደሚቀጥሉ  ድጋፉን ለሰሜን  ጎንደር ሎጅስቲክ  ቢሮ  ያስረከቡት  የኢትዮ  ቴሌኮም  ሰራተኛ  አቶ  ሃይለሚካኤል  አለሙ ገልጸዋል ።

(በታሪኳ መንግስተአብ)